የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1- አላቂ ዕቃዎች
ሎት 2- የደንብ ልብስ
ሎት 3- የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 4- የህትመት አገልግሎት
ሎት 5- የቢሮ መስተንግዶ አገልግሎት
ሎት 6- የትራንስፖርት አገልግሎት
ሎት 7- የቢሮ ላተራልና ፈርኒቸር ጥገና
ሎት 8- ቋሚ ዕቃዎች
ሎት 9- ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
ሎት 10- የዲኮርና ሞንታርቦ እና ድንኳን ኪራይ
ሎት 11- የተሽከርካሪ ጎማዎች
ሎት 12- የሶሻል ካፌ መስተንግዶ አገልግሎት
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- ከዘርፉ ጋር ተያያዥ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከ100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ከተጫረቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ አለባቸው።
- ጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁትን የምናስተናግደው ባመረቱት ምርት ብቻ በመመሪያው መሰረት ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስረከቢያ ጨረታውን ባሸነፈበት መጠን ልክ 10% ማስያዝ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 0.5 ማለትም ሎት1፡ 2000፤ ሎት2፡ 1500፤ ሎት3፡ 2000፤ ሎት4፡2000፤ ሎት5፡ 1000፤ ሎት6፡ 1000፤ ሎት7፡ 1000፤ ሎት8፡ 1000፤ ሎት9፡ 1000፤ ሎት10፡ 2500፤ ሎት11፡ 1000 እና ሎት12፡ 1000 በሚል pay/order Addis Ketema K/K Wereda 10 F/TS/BET በሚል ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለዕቃዎች ማለትም ለሎት1,2,3 ሳምፕል ማቅረብ እና ለቀሪው ሎት በተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ሳምፕል ያልቀረበበትን ዕቃ የማናወዳድር መሆኑን እየገለፅን ሳምፕሉ ጨረታው ከመከፈቱ ቢያንስ ከ3ቀን በፊት መቅረብ አለበት ከተጠቀሰው ቀን ዘግይተው የሚመጡ ሳምፕሎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የሚገቡት ዋጋዎች ቫት/ቲኦቲን ያካተቱ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበት ዋጋ ከላይ የተጠቀሱትን ደጋፊ ሰነዶች 1 ኦሪጅናልና 1 ኮፒ በአንድ ላይ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በተዘጋጀው የማወዳደሪያ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ በወረዳው ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ /ማቅረብ/ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን የጨረታ አይነት ውል አልገባም ቢሉ ውል ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ የሚደረግ እና ለ6 ወር የትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት እንዳይሳተፉ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አጠና ተራ ከድልድዩ ከፍ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፡- 0112739821 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
