Tender Detail

Tender Details

  • Company Semera Customs Branch Office (ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሰመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 366 2302
  • Websitehttp://www.ecc.gov.et/
  • Deadline24 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) የማይመለስ
  • opening date በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Textile, Garment & Leather , Electronics Materials

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ ዘርፍ የጨረታው ዓይነት ዕቃው ያስቀመጠበት ቦታ
1 የፅዳት ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
2 አልባሳት ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
3 ኤሌክትሮኒክስ ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
4 ኮስሞቲክስ ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
5 ጫማ ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
6 ፕላስቲክ ሸራ ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
7 መለዋወጫዎች ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
8 የእጅ ሰዓቶች ግልጽ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
9 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
10 ፓኪንግ ማሽን ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
11 ያገለገሉ መገናኛ መሣሪያዎች ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
12 ጫማ ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
13 ኮስሞቲክስ ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን
14 ኤሌክትሮኒክስ ሐራጅ ጨረታ በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ከሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡ በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
  2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00- 5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ የመንግሥት ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ያገለገሉ መገናኛ መሣሪያዎች ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)፤ ጫማ (ምድብ 01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤ ጫማ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤ ኤሌክትሮኒከስ (ምድብ 01) 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፤ ኤሌክትሮኒከስ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ኮስሞቲክስ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ 150 ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሠርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ የቅ/ጽ/ቤቱ ስም የጨረታው አይነት የንብረት መመልከቻ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት ግልጽ ጨረታ እስከ 13/01/2019 14/01/2019. 3:30 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል
2 ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት ሐራጅ እስከ 13/01/2019 14/01/2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ይከፈታል
  1. ጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት 14/01/2019 ዓ/ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  2. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ /ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
  4. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፡፡
  7. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ:-0332401510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Customs Commission's Semera branch invites bids to sell various confiscated goods by open and auction tender, including cleaning supplies, clothing, electronics, cosmetics, shoes, plastic tarps, spare parts, watches, used communication devices, and a packing machine. Bidders need a valid trade license and tax documents.
Save Tender