Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08፣ የቦታው ልዩ ስም ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115579512
  • Website
  • Deadline07 Oct 2019, 8:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • opening dateመስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Ict Equipment'S And Its Accessories

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረት ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን፡-


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር  AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/G001/2019

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን፡-

ምድብ አንድ፡ የቢሮ (የጽሕፈት) እቃዎች

ምድብ ሁለት፡ አላቂ የጽዳት እቃዎች

ምድብ ሶስት፡ የስራ ልብስ እና ጫማ

ምድብ አራት፡ የኮምፒውተር እቃዎች እና ተያያዥ እቃዎች

ምድብ አምስት፡ ሕትመት

ምድብ ስድስት፡ የተለያዩ የቢሮ ብረት ሼልፎች እና

ምድብ ሰባት፡ የኤሌክትሪክ እና የኢንተርኔት አቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን ዲቪዥን ጽ/ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ በኤሌክትሮኒክስ ማስተላለፍ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN) ሰርትፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ሰ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ACPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋርም በኤሌክትሮኒክ ትራንስፈር ለምድብ አንድ፣ ሁለት እና ሶስት ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፣ ለምድብ አራት እና አምስት ለእያንዳንዳቸው ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)፣ ለምድብ ስድስት ብር 35,000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር)፣ ለምድብ ሰባት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  4. አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈባቸው የዕቃ ዝርዝር የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን 20% ሊጨምር ወይም 20% ሊቀንስ ይችላል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ሰ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  8. ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ 8:30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን አንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
  10. ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ልደታ ከተማ ወረዳ 08፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፦- 251 11 557 90 36 (5ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Water and Sewerage Authority's Water and Sanitation Infrastructure Development Division seeks suppliers for office stationery, cleaning consumables, work uniforms and shoes, computer equipment and accessories, printing, office metal shelves, and electrical and internet materials via national competitive bidding.
Save Tender