Tender Detail

Tender Details

  • Company በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ አምባ አፀደ ህፃናት የመ/ደ/ት/ቤት
  • Address አዲስ አበባ, Phone: 011-4-42-04-41
  • Website
  • Deadline21 Sep 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ)
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 10 ቀን ቆይቶ በ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Stationery Materials

በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ እቃዎች፤ አላቂ የቢሮ አቃዎች፤ አላቂ የትምህርት አቃዎች፤ የፅዳት አቃዎች፤ የደንብ ልብስ፤ የጥገና አቃዎች፤ ቤተ-መጻህፍት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ እቃዎች፤ አላቂ የቢሮ አቃዎች፤ አላቂ የትምህርት አቃዎች፤ የፅዳት አቃዎች፤ የደንብ ልብስ፤ የጥገና አቃዎች፤ ቤተ-መጻህፍት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትሳተፉ አንጋብዛለን፡፡

  1. እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም የተመዘገቡበትን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ከአዲስ አምባ የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ከፍል ቀርበው በ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይገላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በገዙበት የጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት (VAT) ማካተት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ 4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. ከጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ሲያመጡ የተደራጁበትን ዘርፍ ተጠቅሶ ቀጥታ በት/ቤቱ ስም ማናፍ አለበት፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሰነድ መግዣ ዋጋ እና የውል ማስከበሪያ በነፃ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቅሶ መናፍ አለበት፡፡
  12. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አዲስ ሰፈር ድልድይ ወረድ ብሎ አዲስ ሰፈር ጣና ገበያ ፊት ለፊት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09-42-04-41 | 09-70-70-17 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Amba Orphanage and Primary School seeks suppliers for fixed assets, consumable office and educational materials, cleaning supplies, uniforms, maintenance items, and library materials. Bidders must have a valid renewed business license, be registered on the suppliers list, be VAT-registered, and provide samples.
Save Tender