በሸገር ከተማ አስተዳደር በቡራዩ ከፍለ ከተማ የገፈርሳ ቡራዩ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መስሪ ቤቶች እና ለማዘጋጃ ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት የሚውል፡-
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በሸገር ከተማ አስተዳደር በቡራዩ ከፍለ ከተማ የገፈርሳ ቡራዩ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መስሪ ቤቶች እና ለማዘጋጃ ቤቶች ለ2019 የበጀት ዓመት የሚውል፡-
- የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የሠራተኛ ደንብ ልብሶች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና
- የቢሮ ፈርኒቸሮች የሚገልጽ ሰነድ (ዶክመንት) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ዝርዝር ሁኔታዎች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ ዕቃዎቹ የሚገልጽ ሰነድ (ዶክመንት) የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ገፈርሳ ቡራዩ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል የገፈርሳ ቡራዩ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፍ ህጋዊ የታደሠ የንግድ ፍቃድ በስማቸው ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው። እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ ስለመኖሩ የተጻፈለት ደብዳቤ ጋር ሲፒኦ(cpo) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ። የውል ማስከበሪያ (ዋስትና)10 ፐርሰንት ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጨረታ መስፈርት የምታሟሉ የቴከኒክ ፖስታ በኦሪጂናል እና በኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች መጫረት የምትችሉት ህጋዊ ደረሰኝ በብርሃን እና ሰላም (QR) የታተመበት ያላቸው ብቻ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦሪጂናል እና በኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7/1/2019 ዓ/ም እስከ 27/1/2019 በተከታታይ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አድራሻ ገፈርሳ ቡራዩ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት አስተባባሪ ቢሮ/ሲሳይ ህንፃ/ላይ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጽ/ቤቱ ማንኛውም ዶክመንት ከኦሪጂናል ዶከመንት ጋር የሚያመሳከር መሆኑ ግድ እንደ ሆነ እናሳውቃልን።
ለተጨማሪ መረጃ፡-የገፈርሳ ቡራዩ ገንዘብ ጽ/ቤት
በሸገር ከተማ አስተዳደር በቡራዩ ክፍለ ከተማ የገፍርሳ ቡራዩ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Gafarsa Burayu Finance Office seeks suppliers for office supplies, cleaning materials, staff uniforms, electronics, and office furniture for sector offices and municipalities. Bidders must hold a valid business license, tax identification, VAT registration, and be registered on the federal or Oromia supplier list.
