Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቱፋ ሙና ቀ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline26 Sep 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/
  • opening date በ11ኛው ቀን 3፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በጉለሌ ከ/ከተማ ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ፣ ድጎማ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2019

በጉለሌ ከ/ከተማ ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ፣ ድጎማ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ሎት 2 የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ ማሰፊያ ሎት 4 አጋዥ መፅሐፍት ሎት 5 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌትሪክ እቃዎች ሎት 7 የኮምፒውተርና ፕሪንተር ጥገና ሎት 8 የህትመት ስራዎች፣ ሎት 9 ቋሚ እቃዎች ሎት 10 የጥገና ስራ ሎት 11 የካፌ አገልግሎት ግዥ ሎት 12 የጭነት አገልግሎት እና ሎት 13 የአላቂ የትምህርት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. የንግድ ምዝገባ፣ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat 15%/ ተመዝጋቢ የሆናችሁ።
  2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋውን ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው አቅርቦቶች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።
  5. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ለሎት 2 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 4 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 5 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 6 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 7 ብር 1,000.00 ብር /አንድ ሺህ ብር/ ለሎት 8 ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለሎት 9 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 10 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 11 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 12 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ እና ለሎት 13 ብር 5,000.00 ብር አምስት ሺህ በባንክ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ልዩ አስተያየት የሚኖረው አምራች በሆኑበት እቃዎች ላይ ብቻ ከአደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የመንግስት የስራ ቀን ድረስ ከቢሮ ቁጥር 3 ግዥ ክፍል በመምጣት በመንግስት የስራ ሰዓት በእያንዳንዱ የጨረታ አይነቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል የፋይናንሺያል እና የቴከኒኩን በአንድ ፖስታ እና ኮፒውን በሁለት ፖስታ በማሸግ እስከ 10ኛው የመንግስት የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት በጉለሌ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 3 ፋይናንስ ክፍል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ10ኛው ቀን 11:30 ሠዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡30 ላይ በቢሮ ቁጥር 3 ፋይናንስ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  11. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙናዎችን ቀድመው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  13. መስሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾችን ከመረጠ በኋላ ለሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም። በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7(ሰባት) የቅሬታ ቀን በኋላ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚው አካል ማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል። ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

አድራሻችን፡- ጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 7 በሱሉልታ በር ወደ እንጦጦ ማርያም /እንጦጦ ፓርክ በሚወስደው መንገድ 350 ሜትር ገባ ብሎ ቱፋ ሙና ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-8-19-66-82

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቱፋ ሙና ቀ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Tufa Muna Primary and Secondary School seeks suppliers for 13 lots: stationery, uniforms, tailoring, reference books, cleaning and electrical supplies, computer/printer repair, printing, fixed assets, maintenance, café and transport services, and consumable educational materials. Bidders need a valid business license, TIN, and VAT registration. Samples and supplier certificates are required.
Save Tender