Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የዳግ/ብ/ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የዳግ/ብ/ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

(ሎት 1) የደንብ ልብስ እና የስፖርት አልባሳት

(ሎት 2) አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ የፕሪንተር፣ የፎቶ ኮፒ ቀለሞች እና አላቂ የት/ት ዕቃዎች

(ሎት 3) አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

(ሎት 4) የህትመት ስራዎች እና የህክምና እቃዎች

(ሎት 5) ቆሎ፣ ውሃ እና ኩኪስ

(ሎት 6) ለፕላንት ለማሽነሪ ጥገና እና ህንፃ ተገጣጣሚ የጥገና ዕቃዎች

(ሎት 7) ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።

  1. በዘርፉ ታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ያላቸው።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ።
  4. የአቅራቢዎች ምዝገባ ዌብሳይት ያላቸው።
  5. ናሙና /ሳምፕል/ ለሚጠይቁ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ

    ሎት 1፡ 3500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር) (0.5)

    ሎት 2፡- 4500 (አራት ሺህ አምስት መቶ ብር) (0.5)

    ሎት 3፡ 4000 (አራት ሺህ ብር) (0.5)

    ሎት 4፡- 2700 (ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ብር) (0.5)

    ሎት 5፡- 1230 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ) (0.5)

    ሎት 6፡- 5,500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) (0.5)

    ሎት 7፡- 8250 (ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) (ዐ.5) በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በታሸገ ፖስታ ፋይናንስ ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው

  7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ካደራጃቸው አካል ወቅታዊ፤ በፅ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ እና ተጫራቾች የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦ ዋናውን ሰነድ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. የጨረታ ሰነዱ ላይ ተጫራቹ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ክፍል ዘጠኝ ያልተሟላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  10. በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ፋይናንስ ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ዳግማዊ ብርሀን ቁ.2 ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  13. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል ተዋውለው ዕቃዎችን ለት/ቤቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  14. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ አብቅቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ተዘግቶ በእለቱ 3፡30 ይከፈታል።
  15. ጨረታው የማስገቢያው ጊዜ ካበቃ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  16. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የዳግማዊ ብርሀን ቁ.2 ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ብርጭቆ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ዝቅ ብሎ በስተቀኝ በኩል ለበለጠ መረጃ

ስልክ ቁጥር፡- 011 273 1704/ 011 273 1589 / 011 273 1634

የዳግ/ብ/ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks to buy uniforms and sportswear, consumable office and teaching supplies, printer and photocopy toners, cleaning materials, printing services, medical items, food and drinks, machinery and building maintenance supplies, and fixed assets via open tender. Eligible bidders need a valid trade license, TIN, VAT registration, supplier registration, and samples.
Save Tender