በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛና እንስሳት ተዘዋዋሪ በጀት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃ ፈርኒቸር፣ የቢሮ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ብትን ጨርቅና ጫማ፣ የውሃ መስመር መገጣጠሚያ እቃዎች፣ የአነስተኛ ተሽከርካሪ ጎማ፣ የስፖርት ትጥቅ እና ቁሳቀስ፣ የተለያዩ ህትመት እና የጽዳት እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛና እንስሳት ተዘዋዋሪ በጀት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃ ፈርኒቸር፣ የቢሮ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ብትን ጨርቅና ጫማ፣ የውሃ መስመር መገጣጠሚያ እቃዎች፣ የአነስተኛ ተሽከርካሪ ጎማ፣ የስፖርት ትጥቅ እና ቁሳቁስ፣ የተለያዩ ህትመት እና የጽዳት እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው።
- ለእንስሳት መድሀኒት ጨረታ ከእንስሳት መድሀኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን እና ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የመረጡትን እቃዎች ዓይነት፣ ዝርዝር መግለጫ /specification/ እና መመሪያ የያዘ የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤታችን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ አቅርቦት ለእያንዳንዳቸው ከሎት ድምር ዋጋ 1% መቶኛ የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ ትእዛዝ CPO ወይም ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ መሂı ኮፒ ተቆርጦ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በመ/ቤታችን ግዢ ቢሮ ቁ.3 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በብሔራዊ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን። ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ወይም
በስልክ ቁጥር 011-1190-270/280/+251997041395 በመደወል ወይም በtelegram channel @t.me/Ensarowereda ለማየት ዌብ ሳይታችን ለመጎብኘት ensaroweredafinanceoffice@gmail.com ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ 130 ኪ.ሜ ከደብረ ብርሃን በስተ ምዕራብ 83 ኪሜ ወይም በስልክ ቁጥራችን ማግኘት ደችላሉ።
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለሚ
