Tender Detail

Tender Details

  • Company በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ከድሪም ላይነር ሆቴል ወረድ ብሎ ወይም ከናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት የድሮ 35 ቀበሌ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0967670005
  • Website
  • Deadline07 Nov 2026, 4:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityበባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረቱትን ዕቃ ዋጋ ጠቅላላ ድምር በሎት 2 %
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል። 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ::
  • Categories Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች የደንብ ልብሶች ቋሚ ዕቃዎች የጉልበት ስራ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ለአንድ አመት ኮንትራት የሚቆይ የተለያዩ ህትመቶች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 006/002/2019

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች የደንብ ልብሶች ቋሚ ዕቃዎች የጉልበት ስራ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ለአንድ አመት ኮንትራት የሚቆይ የተለያዩ ህትመቶች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ በገ/ኢ/ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር ( supplier List ) ውስጥ የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀትና ማንኛውም ተወዳዳሪ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸው መረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ አስር ( 10 ) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል :: በጨረታ መዝጊያ ሰዓት የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም ::
  4. ተጫራቾች በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃ ዓይነቶች በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ ::
  5. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሊሆን ይገባል ::
  6. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውን እንዲሁም ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም በማህተም ማረጋገጥ ይኖርባል ::
  7. ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩትን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው መፃፍ አለባቸው ።
  8. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ዕቃዎችን ከወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጋር ውል በገባ 10 ቀናት ውስጥ ዕቃ ግምጃቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አገልግሎት ወይም ወጪ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት ::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረቱትን ዕቃ ዋጋ ጠቅላላ ድምር በሎት 2 % በካሽ ማሳያ ማዘዣ እና ኮፒ በተደረገበት የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  10. በጨረታው ያሸነፈው አካል ማሸነፉ እንደተገለጸለት ከመ/ቤቱ ጋር በ10 ( አስር) ቀን ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት ::
  11. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ካልፈጸመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ አይሆንም::
  12. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ሲፈጽም የግዥውን አጠቃላይ ዋጋ 2 % ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል::
  13. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::
  14. የጨረታ ሳጥን በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 10:30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል። 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ::
  15. በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ ለ60 (ስልሳ ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል::
  16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0967670005/0911460014/0913147951/0930649717 በመደወል ከድሪም ላይነር ሆቴል ወረድ ብሎ ወይም ከናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት የድሮ 35 ቀበሌ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Kirkos Sub-City Woreda 02 Administration seeks legal suppliers for office stationery, uniforms, fixed assets, labor services, electronic maintenance, and various printing under a one-year contract. Bidders must hold a valid trade license, be VAT-registered, and appear on the supplier list. Samples required per item; partial or full bids allowed.
Save Tender