በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አላቂ ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አላቂ ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ቦ/ክ/መ/11/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው
- ለትራንስፖርትና ለጭነት ተወዳዳሪዎች ህጋዊ መንጃ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የባለቤትነት ደብተር /ሊብሬ/ ማቅረብ የሚችል
- ሶስተኛ ወገን/ኢንሹራንሽ ማቅረብ የሚችሉ
- ቦሎ ያላቸውና የታደሰ መሆኑ
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 1 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ወረዳ 11 ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 004 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሰሚት ኮንዶሚንየም ሶስተኛ በር አደባባዩን ወረድ ብሎ
ቦሌ ክፍል ከተማ 11/ፋ/ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118 93 15 22
ሎት ቁጥር ሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢት ብር
ሎት 1 የደንብ ልብስ 4,500.00 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/
ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች 4,000.00 /አራት ሺህ ብር/
ሎት 3 የጽዳት እቃ 5,000 /አምስት ሺህ ብር /
ሎት 4 ልዩ ልዩ 3,800 /ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ብር/
ሎት 5 የመኪና ጎማ 10,000 /አስር ሺህ ብር/
ሎት 6 መስተንግዶ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/
ሎት 7 ህትመት 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/
ሎት 8 የፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 9 ትራንስፖርት አገልግሎት 2,800 /ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር/
ሎት 10 የጭነት አገልግሎት 2,800 /ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር/
ሎት 11 ዲኮር እና ድንኳን ኪራይ 4,800 /አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር/
ሎት 12 ጄኔሬተር ኪራይ 2,800 /ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር/
ሎት 13 ስፖርት ትጥቅ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/
ሎት 14 ጀኔሬተር ግዥ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/
ሎት15 የቢሮ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና 2,500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት
