ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ. በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳርና ጂማ በሚገኙ ፕሮጀክቶቹ ላይ ለሲቪል፣ ኤሌክትሪክ፣ ሜካኒካል፣ ሳኒተሪ፣ የውስጥ ዲዛይን፣ አሉሚኒየምና የማጠናቀቂያ ግንባታ ሥራዎች ብቁ የግንባታ ተቋራጮችን በጨረታ ይጋብዛል።
BEAEKA General Business PLC (ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
የግንባታ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር (ቤአኤካ/ኮን/001/2019)
ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር እንዲሁም በጂማ ከተሞች ባሉ
የተለያዩ ፕሮጀክቶቹ ላይ የሚከተሉትን ሥራዎች፡-
- አጠቃላይ ለሁሉም የሲቪል ግንባታ ስራዎች
- የኤሌክትሪክ ስራዎች
- የመካኒካል ስራዎች
- የሳኒተሪ ስራዎች
- የውስጥ ዲዛይን ስራዎች
- የአሉሚኒየም ስራዎች እንዲሁም ሁሉንም የማጠቃለያ ግንባታ ስራዎች (All finshing works) ለማሰራት የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
2. ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ.የተ.ግል ማህበር ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸውን ሥራ ለማሰራት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የግንባታ ሥራ ተቋራጮችን መጋበዝ ይፈልጋል፡-
- በዘርፉ የተሰማሩ
- የ 2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- በዘርፉ ቢያንስ 2 ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት ከሠሩባቸው ድርጅቶች የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ይህንን ሥራ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች
3. ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ተጫራቾች በተ.ቁ7 በሚገለጸው በድርጅታችን ዋና መ/ቤት በአካል በመገኘት መጠየቅ የሚችሉ ይሆናል።
4. ተወዳዳሪዎች የድርጅታቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና የቀድሞ የስራ አፈጻጸም የሚያሳይ ሰነድ (Company Profile) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያቀርቡት ሰነድ (1) ኦርጅናል መሆን አለበት።
5. ተወዳዳሪዎች ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለጸውን ሰነድ ሲያቀርቡ የቴክኒክ ግምገማ የሚደረግ ሲሆን፣ ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ብቻ ለሥራው የዋጋ ማቅረቢያ እንዲሞሉ ይደረጋል።
6. ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተገለጸው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት በአካል በመገኘት ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ.ተ.የግል ማህበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ.የተ.የግል ማህበር ዋና መ/ቤት
ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ሳርቤት
አደባባይእልልታ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
ምህንድስና ክፍል
