በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የጽህፈት እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመብራት እቃ፣ የቧንቧ እቃ፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የመኪና ጎማና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ (ፈርኒቸር/፣ የግንባታ እቃ፤ ሶፍትዌር፣ መድሃኒቶች የህከምና መሳሪያዎች እና መለዋወጫዎች፣ የላብራቶሪ ማሽኖችንና የኤክስሬይ ማሽኖችን ጥገና እና ሰርቪስ የእጅ ዋጋ፣ የአጥር ጥገና፣ የህንጻ እድሳትና ጥገና እና የጭነት መኪና ኪራይ ማውረጃና መጫኛን ጨምሮ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የጽህፈት እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመብራት እቃ፣ የቧንቧ እቃ፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የመኪና ጎማና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ (ፈርኒቸር/፣ የግንባታ እቃ፤ ሶፍትዌር፣ መድሃኒቶች የህከምና መሳሪያዎች እና መለዋወጫዎች፣ የላብራቶሪ ማሽኖችንና የኤክስሬይ ማሽኖችን ጥገና እና ሰርቪስ የእጅ ዋጋ፣ የአጥር ጥገና፣ የህንጻ እድሳትና ጥገና እና የጭነት መኪና ኪራይ ማውረጃና መጫኛን ጨምሮ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ።
- በሙያው ዘርፍ (በሚመለከተው በንግድ ስራ) የተሰማራና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ያላቸው፣
- የግዥ መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታችሁን ማስረጃ ፎቶ ኮፒና ኦሪጅናል ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃወች በናሙናው መሰረት ማቅረብ የሚችሉ/ ናሙናውን ከመ/ቤቱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ በመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱ ላይ ቫትን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመልስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ ከደቡብ ወሎ ዞን ከለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆ/ል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 41 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ የባንክ ዋስትና ከሆነ ከ90 ቀናት በታች መሆን የለበትም፡፡
- የውል ማስከበሪያ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ 10 % ማስያዘ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በጥንቃቄ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ማህተም በማድረግ እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል፣ የጨረታ ሳጥኑ 5፡15 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 38 በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታው በሎት (በጥቅል ዋጋ) የሚወዳደር ይሆናል፡፡
- እቃው ገቢ የሚሆንበት ቦታ ደቡብ ወሎ ዞን አቀስታ ከተማ አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ነው።
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የስራ ዘርፍ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢፈልግ አቀስታ ጠቅላላ ሆ/ል ቢሮ ቁጥር 36 ድረስ በአካል በመገኘት ይችላሉ፡፡ (በቢሮ በስልክ ቁጥራችን 033-1-14-03-66/ 09-27-40-37-36/ 09-15-54-10-90 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ሆ/ሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች አቤቱታ ካላቸው ውጤቱ በተገለፀ በተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ላወጣው ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መድሃኒት የህክምና መሳሪያ ጥገናና ሰርቪስ፣ ሶፍትዊር፣ የመኪና ጭነት ኪራይ ለአንድ አመት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ሁሉም ጨረታ በሎት/ በድምር ዋጋ የሚወዳደር ይሆናል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ ለአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል
