በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን በቢሎ ኖጳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን የቢሎ ኖጳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን በቢሎ ኖጳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የጽህፈት መሳሪያ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የጽዳት እቃዎች
- የሞተር ሳይክል
- የሠራተኛ ደንብ ልብስ
- የተለያዩ ጎማዎች ከእነ ከለመዳሪ
- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች / Furniture/
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- በስራው ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የ2017 ግብር ከፍሎ ፍቃዱን አሳድሶ ያጠናቀቀ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ያለው የሻት) ወይም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በሲፒኦ (Cpo) ለእያንዳንዱ ዶከመንት ማስያዝ የሚችል
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ከቢሎኖጳ ወረዳ ገ/ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
- የሚወዳደሩበት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት ስርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልፅ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ ፍቃድ እና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን አያይዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ሆነው የተመረጡ የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአስር ቀናት ውስጥ በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች የዕቃ ዝርዝር ጨረታ መወዳደሪያ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫት ጨምሮ ወይም ያለቫት በማለት በመጨረሻው ገጽ ላይ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል መስሪያቤቱ የዕቃውን ብዛት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- የሰራተኛ ደንብ ልብስ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የእቃውን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- በራሱ ወጪ ወይም ትራንስፖርት እስከ ቢሎ ኖጳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አቅርቦ ማስረከብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዋጋ በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በቢሎ ኖጳ ወረዳ ገንዘብ ት/ጽ/ቤት እስከ 15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ08/12/2017 ዓ.ም እስከ 28/12/2017 ዓ.ም ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ29/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ29/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0928838278/0917854382
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን የቢሎ ኖጳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
