Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia regional state justice Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ)
  • Address ሀላባ ቁሊቶ ከተማ : ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046556250-
  • Websitehttps://www.cerjustice.gov.et/
  • Deadline13 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበነጻ
  • Bid Securityብር 20,000 (CPO)
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ የእስቴሽነሪ፣ የጽዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

Central Ethiopia regional state justice Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ የእስቴሽነሪ፣ የጽዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ ተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
  5. የጨረታ ሰነዱን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች የተጨማሪ እሴት ታክስን በማካተት በሰም በታሸገ ኤቨሎፕ (ፖስታ) በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046556250 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በማእ/ ኢት/ ክልላዊ መን/ የፍትህ ቢሮ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Regional State Justice Bureau seeks to procure stationery and cleaning materials via open tender. Eligible bidders must hold a valid business license, provide tax payment evidence, be VAT-registered with a TIN certificate, and be registered on the Ministry of Finance or regional supplier list.
Save Tender