Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ /ደሴ ማረሚያ ቤት/ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ነገሮችን እና የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የደሴ ማረሚያ ቤት


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ /ደሴ ማረሚያ ቤት/ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል፡-

  1. የምግብ እልህ ቀይ ማሽላ ፤ነጭ ማሽላ፣ አተር ክክ፣ ተቆልቶ የተከካ የሽሮ ባቄላ፣ ተቆልቶ የተከካ የሽሮ ጓያ፣ ዛላ በርበሬ፣ የዳቦ ፌኖ ዱቄት የሀገር ውስጥ፣ ቅመማ ቅመም፣ የወጥ የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት፣ ዝቃቅቤ ወዘተ የመሳሰሉት ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ የልብስ ሣሙና፣ የእታ ማጠቢያ ሣሙና /አጃክስ/፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ፣ የዳቦ እርሾ፣ የመሳሰሉት፣
  2. የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ህትመት፣ ቋሚ እቃ፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች፤ ህንፃ መሳሪያዎች ፣ የልብስ ስፌት እቃዎች የመሳሰሉት ማቅረብ የሚችሉ ነጋዴዎችን የምግብ ግብዓቶችን እንደየ ሁኔታው ለአንድ አመት በማጫረት ከአሸናፊው ጋር ውል መያዝ ይፈልጋል።

ስለዚህ:-

  1. ለሁሉም የስራ ዓይነት በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  2. ለሁሉም የስራ ዓይነት በየዘርፉ የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ጨረታው በሚከፈትበት እለት የሚጫረቱበትን የእህል ዓይነትና ዛላ በርበሬ ናሙና ከ50 ግራም ያላነሰ ይዞ መቅረብ ያልቻለ ተጫራች በጨረታው መጫረት አይችልም፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ብዛት የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር በአንድ ዓመት አባዝተው የዚያን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/በአማርኛ የተተረጐመ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 ማስያዝ ይኖርበታል።
  5. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ የሁሉም የስራ ዘርፍ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ከደሴ ማረ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ከፍሎ መውሰድ ይችላል፣
  6. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በደቡብ ወሎ ደሴ ማረሚያ ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጐ 9:00 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ታሽጐ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
  8. የጨረታው አሸናፊ በአሸነፉት መሰረት ውል ባይወስዱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል። አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ያሸነፉበትን እቃ ማረ/ቤቱ ድረስ በራሱ ወጭ ያስረክባል፣
  9. አንዱ ባቀረበው የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ሌላው ማቅረብ የለበትም፤
  10. አቅርቦቱን በተመለከተ ከወጥ ሽንኩርት በስተቀር ማረ/ቤቱ በሚፈልገው መጠንና ልክ መሠረት ወር ከመግባቱ በፊት ከ25-30 ቀን ድረስ የወሩን የምግብ ፍጆታ አጠቃሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  11. የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% የአንድ አመት ጠቅላላ ዋጋ የሚያሲዝ ሲሆን ተጫራቾች ማብራሪያ የሚፈልግ ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0331116516 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ለሚያደርጉት ግብይት ህጋዊ የሆነ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለበት።
  13. ለታራሚዎች በአማካይ በየወሩ የሚቀርብ የምግብ እህል ፣ ቅመማ ቅመም ፣ ወዘተ... ብዛት በአማካይ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፣
  14. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ቫት ያላቸው ግብይቶችን በምንፈጽምበት ጊዜ ለመንግስት 7.5% ቆርጠን የምናስቀር መሆኑን እንገልጻለን።

 

በደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የደሴ ማረሚያ ቤት

 

Save Tender