የአርሲ ዞን ሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአርሲ ዞን የሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁ-01/2018
የአርሲ ዞን ሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾቾ ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለጽሕፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) እንዲሁም፣ ለጽዳት እቃዎች፣ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000062690023 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽሕፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች፣ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ሥሬ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0223300408/0913910056) ይጠይቁ፡፡
በአርሲ ዞን የሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
