በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን አራብሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ላሉት ለመንግሥት መ/ቤቶች ለ 2018 ዓ.ም ለአንደኛ ዙር የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የሠራተኞች ደንብ ልብስ ፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፤ የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ የግንባታ እቃዎች ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ የሕትመት ሥራዎች እና ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2018
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን አራብሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ላሉት ለመንግሥት መ/ቤቶች ለ 2018 ዓ.ም ለአንደኛ ዙር የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የሠራተኞች ደንብ ልብስ ፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፤ የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ የሕትመት ሥራዎች እና ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የ2016 ዓ.ም የከፈሉና የ2017 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ከ22/11/2017 ዓ.ም እስከ 12/12/2017 ዓ.ም ድረስ ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ ላይ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር / ከፍለው ከገላን አራብሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ላለፉት ዓመታት ማለትም በ2016 ዓ.ም እና በ2017 ዓ.ም አንደኛ ዙር ግዢ ላይ በአቅራቢነት ችግር ያልፈጠሩ ጥሩ የአቅራቢነት ባህሪይ ያላቸው መሆኑን ከፌዴራል ወይም ከክልል ወይም ከከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥ መ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ንግድ ዘርፍ 0.5% ጠቅላላ ዋጋውን ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን "Specification" ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋው ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 12/12/2017 ዓ.ም ድረስ በተዘጋጀው ሣጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ10፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በ13/12/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይንም ወኪላቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታው ሳጥን ከታሸገ ወይንም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ከውል ሰጪ መሥሪያ ቤት ጋር በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት ገላን አራብሳ ለሚገኘው በውል ሰጪ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
- መ/ቤታችን በሚያወዳድረው እቃዎች ብዛት ላይ እንደ አስፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች እቃዎቹን አሸንፈው ለማቅረብ ሲዋዋሉ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለጸ ከ5 ቀን በኋላ በውል ሰጪ መሥሪያ ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት መፈጸም አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913015117/0922334486
የገላን አራብሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
