Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት 01 የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 02 ቋሚ እቃ/ፈርኒቸር/ ሎት 03 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ሎት 04 የፅዳት እቃዎች ሎት 05 ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች ሎት 06 የመኪና ጎማ ሎት 07 የመኪና ዘይት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ከብር 500000 /አምስት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መከፈቻው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመከፈል 07/1/2019 እስከ 16/01/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው 1. ከወጣበት ከ 07/1/2019 ዓ.ም እስከ 16/01/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በ17/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. አሰፈላጊ ለሆኑ እቃዎች መምሪያው ሳምፕል የሚያቀርብ በመሆኑ ሳምፕሉን በጥንቃቄ በማየት እቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሠሪው መሥሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ከ5 /አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09135 09999 ደውሎ መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል፡፡
  13. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመሥሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል፡፡
  14. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  15. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  16. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Kombolcha City Administration Finance Department seeks bidders for office supplies, furniture, electronics, cleaning materials, vehicle consumables, tires, and oil, in 7 lots. Bidders need a valid trade license, tax payment proof, and TIN certificate; VAT registration required if purchase exceeds 500,000 birr.
Save Tender