በጉለሌ ክ/ከተማ የሠላም ጤና ጣቢያ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የመኪና ኪራይ፣ ህትመት፣ ሪኤጀንትና መድሃኒት፣ የካፌ አገልግሎትና ቋሚ ዕቃ ግዥ በ12 ሎት ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 002/2019)።
በጉለሌ ክ/ከተማ የሠላም ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ 002/2019
በጉለሌ ክ/ከተማ የሠላም ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያገለግሉ የጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የልዩ ልዩ ዕቃዎች፣ የመኪና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የተለያዩ የቢሮ ፓርቲሽን ጥገናዎች፣ ህትመቶች፣ መድሃኒቶችና ሬኤጀንቶች፣ የመኪና ኪራይ፣ የሰራተኛ የካፌ አገልግሎት እና ቋሚ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም የእያንዳንዱን ጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የማይመለስ ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
| ዘርፍ | የሰነድ ዋጋ (ብር) | የጨረታ ማስከበሪያ CPO (ብር) |
|---|---|---|
| ለጽህፈት መሣሪያዎች | 100.00 | 3,000 |
| ለጽዳት ዕቃዎች | 100.00 | 6,000 |
| የደንብ ልብስ | 100.00 | 30,000 |
| የደንብ ልብስ ስፌት | 100.00 | 600 |
| ለልዩ ልዩ ዕቃዎች | 100.00 | 4,000 |
| የመኪና ዕቃዎች | 100.00 | 5,500 |
| የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የተለያዩ የቢሮ ፓርቲሽን ጥገናዎች | 100.00 | 5,000 |
| የመኪና ኪራይ | 100.00 | 1,000 |
| ለህትመት | 100.00 | 9,300 |
| ለሪኤጀንት እና መድሃኒት | 200.00 | 33,000 |
| የሰራተኛ የካፌ አገልግሎት | 200.00 | 20,000 |
| ቋሚ ዕቃ | 100.00 | 24,000 |
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው (መጠኑ ከላይ በሰንጠረዡ ተገልጿል)
- የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከጤና ጣቢያው በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ እንዲሁም ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኮፒ ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች ላይ ቫትን ያካተተ መሆኑ መግለጽ ይኖርባቸዋል ካልተገለጸ ግን ቫትን እንዳካተተ ይቆጠራል፤ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ያላደረገ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ፣አማራጭ ሳምፕል /ዋጋ/ ያቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ካላቀረቡ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ 10ኛ ቀን 11:00 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ እና ሰነድ መግዛት የሚችሉት በተሰማሩበት ዘርፍ ላይ ብቻ ነው።
- ጤና ጣቢያው እንደ አስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የመጣ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልጻለን።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
1. ከእንቁላል ፋብሪካ በላይ በአምቢልታ ሆቴል አስፓልት ከነማ አደባባይ ከፍ ብሎ
2. ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ከጉለሌ ንግድ ባንክ ወደ ወረዳ 9 የሚያስወጣው አስፓልት ከነማ አደባባይ ከፍ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0112593899 / 0112593900
በጉለሌ ክ/ከተማ የሠላም ጤና ጣቢያ
Summary
Selam Health Center (Gulele sub-city, Addis Ababa) tenders 12 lots: stationery, cleaning items, uniforms and tailoring, sundry items, vehicle parts, electronics and partition repair, vehicle rental, printing, reagents and medicines, staff cafe service and fixed assets.
