Tender Detail

Tender Details

  • Company Lion Insurance Company S.C (አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
  • Address ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና አንበሳ ኢንሹራንስ ህንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-352283
  • Websitehttps://www.anbessainsurance.com/
  • Deadline04 Dec 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 20% CPO (ከብር 4,000 በታች ለሆኑ ብር 1,000)
  • opening dateህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት
  • Sector Disposal Sale , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Used Items

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ ንብረቶችና የተለወጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን ለመሸጥ ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ።

Lion Insurance Company S.C (አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

  1. አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን የተለወጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
  2. የመኪናዎቹን የንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ (ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል) በስራ ሰዓት ከህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስገቢያ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 ከቫት በፊት (ሶስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታ እስከሚያልቅበት ቀን ድረስ ከዋናው መ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ ንብረት ዋጋ በኤንቨሎፕ፣ በራሱ የጨረታ ሰነዱን በማሟላት እስከ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚመረጡበት ተሽከርካሪ ንብረት የመነሻ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) መሆኑን እያሳወቅን መነሻቸው ከ 4,000.00 ብር በታች የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች በማስያዣነት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያው ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ጨረታው ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ሙሉ ክፍያ በ 5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል። ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ በ10 ቀናት ንብረቶቹን ካላነሱ ለሃያ ቀናት በየቀኑ ብር 100.00 /መቶ ብር/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከፍለው ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
  8. ለጨረታ ከቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል።
  9. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
  11. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
  12. ጨረታውን በተመለከተ ለሚቀርብ ማንኛውም ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወደ ስማቸው ለማዞር ከተሸጠበት ቀን ጀምሮ እስከ ሶስት ወር ድረስ ወደ ስማቸው ማዞር ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን ኩባንያው በተሽከርካሪው ላይ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር እና ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ኩባንያው ኃላፊነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን።
  14. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-352283 ወይም 0116-187000/6632947 በመደወል ወይም በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)

Summary
Lion Insurance Company S.C. sells accident-damaged heavy and light vehicles, other salvage property and replaced vehicle spare parts by sealed bid. Items can be viewed at its salvage yard in Kality, near the Korki factory.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender