በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የህንፃ ጥገናና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ግዥ በ7 ሎት ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2019)።
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ለመፈጸም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ሎት-1 የደንብ ልብስ ሎት-2 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሎት-3 የፅዳት ዕቃዎች ሎት-4 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-5 ቋሚ ዕቃዎች እንዲሁም 6- የህንፃ ጥገና 7- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስጠገን ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች
- የመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ያለው፣
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 11:30 በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የእቃው ከታች በየሎቱ የተዘረዘረውን ብር በጥሬ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ሲፒኦ(CPO) ተጫራቾች ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊው ያስያዙትን ወዲያውኑ ይመለሳል።
- ጨረታውን ለማባዛት መሞከር ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ጨረታ ማስከበሪያም እንደሚወረሱ ማወቅ አለባቸው።
- ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን በ4:00 ታሽጎ በ11ኛ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀን በ4:30 ሰዓት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ ቀን በሰዓቱ ይከፈታል።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በማንኛውም የመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገደ መሆን ይኖርበታል።
- እስፔስፊኬሽን ላልቀረበላቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርብ ዋናውንና ቅጂውን በሚመለከተው መፈረምና ማህተም መደረግ አለበት።
- በዋጋ መሙያው ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ተቀባይነት የለውም።
- ጥቃቅንና አነስተኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን ዓይነት ምርት እደሚያመርቱ እና ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና የጨረታ ማስረከቢያ ፡ የውል ማስረከቢያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
- ውል የገባው ተጫራች ውሉን በገባበት ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ካላስገባ በየቀኑ የሚታሰብ ውል በገባበት ሂሳብ ልክ 1 ፐርሰንት (1%) የሚታሰብ ቅጣት አለው። ለሎት- 1 ብር 25,000፣ ለሎት2 ብር 15,000፣ ለሎት-3 ብር 18,000፣ ለሎት- 4 ብር 15,000፣ ለሎት-5 ብር 25,000፣ ለሕንፃ ጥገና -6 ብር 17,000፣ ለኤሌክትሮኒክስ ጥገና -7 ብር 15,000 ተጫራቾች ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ሙሉን ሰነድ ሳይቆራረጥ ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በ2 ፖስታ አሽጋችሁ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎችን በኦርጂናል እና በኮፒው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ሊያቀርቡ ይገባል፤ የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ፋይናን ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 ይሆናል እንዲሁም ናሙና መረከቢያ ጊዜ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት እስከ 4:00 ይሆናል።
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አንዶዴ የመ/ደ/ት/ቤት ቴሌ ግምጃ ቤት ባለው መንገድ ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ 011- 435- 20 69/70
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአንዶዴ የመጀ/ደ/ት/ቤት
Summary
Andode Primary School (Akaki Kality, Addis Ababa) buys goods and services in 7 lots: uniforms, consumable school supplies, cleaning items, office consumables, fixed assets, building repair and electronics repair. Registered, licensed, VAT-registered suppliers may bid.
