Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የፅህፈት መሳሪያ፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መስተንግዶና የደንብ ልብስ በ7 ሎቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

በአብክመ በደወ/ዞን የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም:- ሎት:-1 ፅህፈት መሳሪያ ሎት:-2 ህትመት ሎት:- 3 የፅዳት እቃዎች ሎት4:- አላቂ ቋሚ የቢሮ እቃዎች ሎት:- 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 6:- መስተንግዶ ሎት:- 7 ደንብ ልብስ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በቀን 09/03/2019 ዓ.ም የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ተወዳዳሪዎች በግብር ዓመቱ ተገቢውን የታክስና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ግዥው የተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለከተው ካልሆነ በስተቀር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የግዥ መጠኑ ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ተጫራቾች የተሰጠውን የጨረታ ቅፅ በአግባቡ መሙላት የሚችሉ፤
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ተራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-4 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ከሎት1-7 ላሉት ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብቻ የእቃውን ጠቅላላ ግዥ ግምታዊ ዋጋ 2% ብር 8500 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታ ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 09/03/2019 ዓ.ም አንስቶ ለተከታታይ 10 ቀናት በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍቤት ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ዘወትር በስራ ሰዓት 11:30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነዱን በመለየት በተለያየ ፖስታ በማሸግ በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በሚገኝበት ከመነሀሪያ ገባ ብሎ ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሮችን በግዥ ፋን/ አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ማስገባት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 09/03/2019 እስከ18/03/2019 ዓ.ም 30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 21/03/2019 ዓ.ም ከጧቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ተራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  11. አስፈላጊ ለሆኑ እቃዎች ፍርድ ቤቱ ሳምፕል የሚያቀርብ በሆኑ ሳምፕሉን በጥንቃቄ በማየት እቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  12. የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።
  13. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ቀን 5 (አምስት ) ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 311 1010 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  14. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል።
  15. ጨረታውን ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል።
  16. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።
  17. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20 (ሀያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  18. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ንብረት ክፍል በራሱ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ ያለው መሆኑን ይህ ሲባል ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።

በአ.ብ.ክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

Summary
Dessie Zuria Woreda Court (Amhara) buys in 7 lots: stationery, printing, cleaning items, office consumables and furniture, electronics, catering items and uniforms, by national open tender. Licensed suppliers with tax clearance and VAT may bid.
Save Tender