በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የህክምና ቁሳቁስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስ፣ የህንፃ መሳሪያና የላቦራቶሪ ኬሚካል በ8 ሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚገኘው የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ ቁሳቁሶችን
- የፅህፈት መሳሪያ (ሎት 1)
- የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 2)
- የህክምና ቁሳቁስ (ሎት 3)
- ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 4)
- ፈርኒቸር (ሎት 5)
- የደንብ ልብስ (ሎት 6)
- የህንፃ መሳሪያ (ሎት 7)
- የህምና ሬኤጀንት (ሎት8)
በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
- ተጫራቹ ከጨረታው ዶክመንት ጋር የሚያያይዛቸው ተጨማሪ ዶክመንቶች:-
- አቅራቢው የተሠማራበትን የሥራ ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
- ከተሰማራበት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ስለተሰማራበት የሙያ ዘርፍ በሚመለከተው አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣ ማቅረብ (የቀረበው ማስረጃ በኦንላይን እንዲታይ የቀረበ ከሆነ በኦንላይን የ egp ፖርታል ላይ ካለው ጋር ተናበቢ መሆን ይኖርበታል።)
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጹ መረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚያቀርቡት አጠቃላይ
- የጽህፈት መሳሪያ (ሎት1) ብር 5,000
- የፅዳት እቃዎች (ሎት2) ብር 5,000
- የህክምና ቁሳቁስ( (ሎት 3) ብር 15,000
- ኤሌክትሮኒክስ(ሎት4) ብር 20,000
- ፈርኒቸር (ሎት 5) ብር 20,000
- የደንብ ልብስ( (ሎት 6) ብር 20,000
- የህንፃ መሳሪያ (ሎት7) ብር 10,000
- የላቦራቶሪ እና ፋርማሲ ኬሚካል ፣ ሬኤጀንት እና ማቴሪያል(ሎት8) ብር 20,000
ሀ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም
ለ/ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ወይም
ሐ/ በሲፒኦ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ህጋዊ ማህተም ያለዉ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በቂ ዋስትናና ለዋስትና ሊበቁ የሚችሉ ማስያዣዎች 10% ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመያዝ ሚዛን - አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካውንት ቁጥር 1000040517964 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫስ በማቅረብ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የፋይናንሻልና ቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በተለያዩ ፖስታ በሰም ኢንቨሎፕ በማሸግ ማኅተምእናፊርማ በመፈረም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያ ናሙና እና የፈርኒቸር ናሙና በፎቶ ከመወዳደሪያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎችን ሚ/አ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከሰዓት 8:00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0473360763 መጠቀም ይችላሉ።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መን/ጤና ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
Summary
Mizan Aman Health Science College (Bench Sheko Zone) buys in 8 lots: stationery, cleaning items, medical supplies, electronics, furniture, uniforms, building materials, and lab and pharmacy chemicals and reagents. Licensed suppliers with TIN, VAT and supplier registration may bid.
