Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
  • Address ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 4734508
  • Website
  • Deadline03 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1500(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid Securityሎት 1 100,000፣ ሎት 2 100,000፣ ሎት 3 50,000፣ ሎት 4 50,000 ብር በCPO/ባንክ ጋራንቲ
  • opening dateበዚያው ዕለት ከቀኑ 5:00 ይከፈታል።
  • Sector Printing And Publishing , Catering And Cafeteria Services , Stationery Materials , Freight Transport

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለጤና ቢሮውና ለተጠሪ ተቋማት የጽህፈት መሳሪያ፣ ህትመት፣ ሪፍሬሽመንትና አዳራሽ ኪራይ እና የጭነት መኪና ኪራይ በ4 ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለጤና ቢሮ እና ለተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 ጽ/ማሳሪያ
  • ሎት 2 ህትመት
  • ሎት 3 ሪፍሬሽመንት እና አዳራሽ ኪራይ
  • ሎት 4 የጭነት መኪና ኪራይ

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  • በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀት /TIN Number/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የሦስተኛ ወገን ቦሎ፣ሙሉ ኢንሹራንስ እና ሊብሬ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል

በመሆኑም ተጫራቾች ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት መግዣ የማይመለስ ብር 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ቀርበው በመክፈል ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት 15 /አስራ አምስት ቀናት/ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።

የጨረታ ማስከበሪያ: ሎት 1 ጽ/ማሳሪያ 100,000 ብር /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ፤ ሎት 2 ህትመት 100,000 ብር/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ፤ ሎት 3 ሪፍሬሽመንት እና አዳራሽ ኪራይ 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ፤ ሎት 4 የጭነት መኪና ኪራይ 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም CPO /ባንክ ጋራንቲ/ በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ አስ/ር ዳይሬክቶሬት በማቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ 1 /አንድ/ ኦሪጅናል እና 2/ሁለት/ ኮፒ ፖስታዎች ለየብቻቸው በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻ፣ ማህተምና ፊርማቸውን በግልጽ መሙላት ይኖርባቸዋል።

የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 5:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይከፈታል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

አሸናፊው ድርጅት በተወዳደረበት ቦታ ንብረቱን የማቅረብ ግዴታ አለበት።

ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መ/ቤቱ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0917004484/092412666

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Summary
South West Ethiopia Peoples Region Health Bureau buys in 4 lots for itself and affiliated institutions: stationery, printing, refreshments and hall rental, and truck rental. Licensed suppliers with supplier registration, TIN and VAT may bid; truck owners need libre and insurance.
Save Tender