የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስና የትምህርት ስቴሽነሪ በ2 ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 02/2019)።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2019
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች በሎት የቀረቡትን የትምህርት እቃዎች ግዥ በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም:-
- ሎት 1. የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ግዥ
- ሎት 2. ስቴሽነሪ ግዥ
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለማሳተፍ የሚፈልጉ:-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፤ የተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ፤
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 - 6:00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 9:00 ሰዓት ይከፈታል፤ ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
- ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩ በፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ላይ በማድረግ ከአንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው። የእቃው ናሙና የጨረታ ሰነድ በሚገባበት ወቅት መቅርብ አለበት። ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል።
- ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይቻላል፤ ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 046-221-7002/3
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
Summary
Sidama Region Education Bureau, with UNICEF programme funding, buys in 2 lots: hygiene materials for female students and school stationery. Licensed suppliers with paid taxes, TIN and supplier registration may bid; samples required.
