Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ
  • Address የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ህንፃ 2ኛ ፎቅ, Phone:
  • Website
  • Deadline27 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Bid Securityበሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ፤ መጠኑ ከጨረታ መመሪያ ጋር ተያይዟል
  • opening date4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • Sector Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ስቴሽነሪና የፅዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ እስቴሽነሪና የፅዳት እቃዎችን ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም :-

  • ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ስራ ቀናት ውስጥ ቦታ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል።
  • ይህ ጨረታ በ10ኛው በሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይሆናል።
  • አቅራቢዎቹ የእቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ፎርም ላይ ነጠላ ዋጋውን እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፤ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይገባቸዋል። አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  • ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
  • አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  • ቢሮው የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ 2ኛ ፎቅ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

Summary
Sidama Region Communication Bureau buys stationery and cleaning items by open tender. Suppliers with a renewed trade licence, supplier registration, paid taxes and VAT registration may bid.
Save Tender