Tender Detail

Tender Details


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የውሃ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የላብራቶሪ ዕቃዎችን በ10 ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ግዥ መለያ ቁጥር 18/2019)።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ግዥ መለያ ቁጥር- 18/2019 ዓ/ም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 2 ፈርኒቸር፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ሎት 7 ስፖርት ማስተማሪያ ትጥቅ፣ ሎት 8 የውሃ ዕቃዎች፣ ሎት 9 የመኪና ጎማ እና ሎት 10 የላብራቶሪ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ህጋዊ ብቃት ያላቸው የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው:-

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘርፉ የታደሰ ፍቃዳቸውን ለመታደሱ ማረጋገጫ ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች በቀረበው የዋጋ መሙያ ሠንጠረዥ ሰነድ ላይ የፋይናንሻል ማስረጃ 1/አንድ/ ኦርጅናል እና 1/አንድ/ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ፣ የቴክኒካል ማስረጃ 1/አንድ/ ኦርጅናል እና 1/አንድ/ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ በአንድ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጋዜጣው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከ4:00 በፊት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ከመጫረቻ ፋይናንሻል ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት እሁድ እና ቅዳሜ ጨምሮ ሰነዱን ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኮሌጁ አካውንት ቁጥር 1000053838875 በማስገባት የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 4:00 ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድን ጨምሮ ህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ የስራ አፈጻጸም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት አድራሻ ግ/በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዕቃ ዋጋ ከቫት ጋር ያለው መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ /ሰነድ መሙላት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ ማሻሻል አይቻልም።
  11. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ላቀረቡ ዕቃዎች መሸጫ የሚወዳደሩት በሎት ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
  12. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች የሚያስረክቡበት ቦታ ግ/በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

ለበለጠ መረጃ:- 0948761907፣ 0931842322፣ 0913436703

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

Summary
Gilgel Beles Teachers College (Benishangul Gumuz) buys in 10 lots: electronics, furniture, uniforms, cleaning items, stationery, electrical items, sports kit, water items, vehicle tyres and laboratory items. Domestic suppliers with a renewed licence and VAT may bid.
Save Tender