Tender Detail

Tender Details


በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ህትመቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፣ የደንብ ልብስና የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በ6 ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው ማስታወቂያ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ ሎት2 ጽዳት እቃ፤ ሎት3.ኤሌክትሮኒክስ እቃ፤ሎት 4 ልዩልዩ ህትመቶች ሎት 5. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፤ሎት 6. ደንብ ልብስ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ህጋዊ የሆኑ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል በመሆኑም

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው
  4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
  5. ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፤በእያንዳንዱ ሰነድ ገፅ ላይ ከስራ ዘርፉ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግልፅ የሚነበብ ማህተም መምታት አለባቸው።
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ከቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / Bid Bond / ለእቃው የሞሉትን ለፅህፈት መሳሪያ 4000ብር ለጽዳት እቃ 1000ብር ለህትመት2000ብር ለኤሌክትሮኒክስ እቃ 1500ብር ለደንብ ልብስ 2000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / cpo / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በውስጥ ገቢ ካርኒ አስገብቶ ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው ።
  9. ተጫራቾች በቀረበው ዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ፍ/ቤት የግዥ /ፋ/ን/አስ /ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን እስከ 3:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው ቀን 3:01ሰዓት ታሽጎ 3:30ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሀሳቦች ተቀባይነት የላቸውም። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3:30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል ፤የቫት ተመዝጋቢዎች ዝቅ ብለው ሲወዳደሩ ሰነዳቸው የተሟላ መሆን አለበት።
  11. የጨረታው መክፈቻ በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ።በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0910473819 ፣ 011 13 20 004 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ።
  14. በማንኛውም ግዥ ከብር 20000(ሃያ ሺህ ብር) በላይ ለአገልግሎት ከብር 10000ብር (አስር ሺህ ብር ) በላይ የቅድመ ግብር ታክስ 3% ሶስት ፐርሰንት ተቀንሶ ለመንግስት ይከፈላል።
  15. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻ እና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ መምታት አለባቸው።
  16. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ የሆናሉ ፤ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ይወረሳል፤ በመንግስት ጨረታ ላይ ለሁለት ዓመት እንዳይወዳደሩ ይደረጋል።
  17. ስርዝ ድልዝ ፤ፍቅትያለው ፍሉድ የነካው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  18. የጨረታ አሸናፊዎች እቃውን ፍ/ቤቱ በሚፈልገው ቦታ ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
  19. ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ራሳቸውን ማግለል አይችሉም ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ፍ/ቤት

Summary
Merhabete Woreda Court (North Shewa, Amhara) buys in 6 lots: stationery, cleaning items, electronics, assorted printing, repair of electronic equipment, and uniforms plus office equipment. Suppliers with a renewed licence, TIN, trade registration and tax clearance may bid.
Save Tender