Tender Detail

Tender Details

  • Company ELFORA Agro Industries PLC (ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251116461076
  • Websitehttps://www.midrocinvestmentgroup.com/poultry-products/
  • Deadline25 Nov 2026, 1:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityበእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ) በሲፒኦ
  • opening dateበዚሁ ዕለት በ8:00 ሰዓት ይከፈታል።
  • Sector Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Used Items

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር በቢሾፍቱ፣ በወንጂ፣ በሀዋሳና በጨፋ የሚገኙ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ ጀሪካኖች፣ ማዳበሪያ፣ የእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች፣ ትራክተሮችና የውሃ ፓምፖችን በ5 ሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

ELFORA Agro Industries PLC (ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)


የጨረታ ማስታወቂያ

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ያገለገሉ ዕቃዎች ዝርዝርዕቃው የሚገኝበት ቦታየጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሲ.ፒ.ኦ (ብር)
ቁርጥራጭ ብረቶች ፣ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች የዉሀ ሮቶ እርጎ በርሜል የብረት የተለያዩ የአስቴሽነሪ ዕቃዎች ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ጀሪካኖች ፣ የፕላስቲ ከሬቶች፣ የግሪን ሀዉስ ፕላስቲክ ፣ ፕላስቲክ በርሜል ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ማዳበሪያ፣ የተለያየ መጠን ያላቸዉ የኬሚካል እቃ ፣ የእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች ፣ ትራክተሮች፣ እና የውሃ ፓምፕ ወዘተ እቃዎችሎት 1. ኤልፎራ ቢሾፍቱ ጂቱ(ቢሾፍቱ)
ሎት 2 ኤልፎራ ቢሾፍቱ ፖልትሪና ቁራ (ቢሾፍቱ)
ሎት 3. ወንጂ ኩሩፍቱ (ወንጂ)
ሎት 4. ኤልፎራ ሻሎ እርሻ (ሀዋሳ ሻሎ)
ሎት 5 ጨፋ የተቀናጀ እርሻ (ጨፋ)
በእያንዳዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ)

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾ አዲስ አበባ ላይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ጉርድ ሾላ (ላምበረት) አካባቢ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት መግዛት ይችላሉ የጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ነው።
  3. ተጫራቾች ዋጋ ከመስጠታቸው በፊት ዕቃዎች በሚገኙበት ከተማ በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለጨረታ ማስከበሪያ/Bid bond/ የሚሆን ብር ከላይ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጹትን ፎርማሊቲዎች በማሟላት በዚሁ ፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መለያ ኮድ (ሎት) እና ቦታ በፖስታው ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
  7. ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረጋል።
  8. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር ለ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት በኤልፎራ ዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ገበያና ሽያጭ አገልግሎት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታቸውን እንዲያስገቡ ይደረጋል፤ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 7:30 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል። ከዚያም በዚሁ ዕለት በ8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል።
  9. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-09 54 49 53 63 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር

Summary
Elfora Agro Industries PLC sells used items in 5 lots at its Bishoftu, Wonji, Hawassa Shalo and Chefa sites: scrap metal and sheets, tyres, batteries, jerrycans, plastic crates and barrels, farm tools, tractors and water pumps. Licensed, VAT-registered buyers may bid.
Save Tender