የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገለገሉ ባትሪዎች፣ ጎማዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ ፕላይውድ፣ የጀነሬተርና የኤሌክትሪክ እቃዎች ሽያጭ
Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 06/2026/27
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ከተሽከርካሪ የተፈቱ ብረታ ብረቶች፣ የጣሊያን ስሪት ፕላይውድ (ኮምፖርሳቶ)፣ የጀነሬተር መለዋወጫ እቃዎችን እና የኤሌክትሪክ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል።
- ስለ አሻሻጭ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያገለገሉ ንብረቶችን ከህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የጣሊያን ስሪት ፕላይውድ (ኮምፖርሳቶ)፣ የጀነሬተር ዕቃዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ምድቦች የሚገኙት ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።
- ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ያስገባል ።
- ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲ.ፒ.ኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Summary
Commercial Bank of Ethiopia is selling used vehicle batteries, tyres, scrap metal from vehicles, Italian-made plywood, generator spare parts and electrical items as-is by sealed bid.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
