የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን 1,400 ያገለገሉ የአጥር ቆርቆሮዎችን በመነሻ ዋጋ ብር 350,000 በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ (አ/አ/ከ/መ/ባ/ን/ማ/01/2019)።
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
ያገለገሉ የአጥር ቆርቆሮዎች የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ የአጥር ቆርቆሮዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | ብዛት | የጨረታ መነሻ ነጠላ ዋጋ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ መ/ ቁጥር | ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ | የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
| 1 | ያገለገሉ የአጥር ቆርቆሮዎች | 1,400 /በቁጥር/ | 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ | 350,000.00 | አ/አ/ከ/መ/ባ/ን/ማ/01/2019 | 30 ቀን | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 |
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባለስልጣን መ/ቤቱ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 በመምጣት ብር 100 በመግዛት : በጦር ሃይሎች አጉስታ አካባቢ በሚገኘው የባለስልጣን መ/ቤቱ ፕ/ጽ/ቤት በመሄድ፣ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ።
- የተጠቀሰውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙትን ዋጋ በኤንቬሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ቀን ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ጀርመን አደባባይ በሚገኘው በባለስልጣን መ/ቤቱ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያስረዳ ህጋዊ ሰነድ የነዋሪነት መታወቂያ ፓስፖርት ወይም ፋይዳ ምዝገባ ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ጀርመን አደባባይ በሚገኘው በባለስልጣን መ/ቤቱ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድር ራሳቸውን የሚያገሉ ወይም ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀባቸው በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆኑበትን ጠቅላላ ዋጋ መክፈል ይኖርባቸዋል።
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ
ስልክ ቁጥር 09-15-56-67-91/0911793645
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
Summary
Addis Ababa City Roads Authority sells 1,400 used corrugated-sheet fence panels by tender. Items can be inspected at its project office near Tor Hailoch. Open to individuals and firms with a valid ID, residence card, passport or Fayda registration.
