Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም. የስልጠና፣ የቢሮ፣ የፅዳትና ቋሚ ዕቃዎችን እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለኮሌጁ የሚያገለግሉ ለስልጠና ዕቃዎች፤ ለቢሮ ዕቃዎች ለፅዳት ዕቃዎች የቋሚ ዕቃዎችና ለደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ:

ሀ/ የተወዳዳሪዎች መመሪያ

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚገልጽ መሆኑንና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ በቂ ማስረጃ ከመወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው ።
  2. ማንኛውም ተጫራች ከ100,000(አንድ መቶ ሺህ) የግዥ ግምት በላይ የሚጫረት ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ መሆን አለበት ።
  3. ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስናና የብክነት ድርጊቶች ነፃ የሆነና በፌዴራልና በክልል የወጡትን የግዥ መመሪያ እና ደንቦችን የሚያከብሩ ስለመሆኑ ሰነዱ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምኖበት መፈጸም ይኖርባቸዋል ።
  4. ከጨረታ ሰነድ ጋር የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ፤
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት ) ቀናት የጨረታ ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ በስራ ሠዓት በኮሌጁ ጽ/ቤት በመገኘት ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይቻላል ።
  6. ጨረታውም በወጣ በ15ኛው ቀን ልክ በ11:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ስሆን ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ) ብር በሲፒኦ ማስያዝ አለበት ።
  7. አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን ኮሌጁ ድረስ በራሱ ወጪ ማድረስ የሚችል
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለዝርዝር መረጃ :- ስልክ ቁጥር 0913649578/ 011 187 05 98 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Gohatsion Technical and Vocational Training College, Wara Jarso Woreda, North Shewa, Oromia, buys training materials, office items, cleaning items, fixed items and uniforms by open tender. Bidders need a renewed sector licence, supplier registration, paid tax, VAT and TIN.
Save Tender