Tender Detail

Tender Details


የሀረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ እቃዎችና የግንባታ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቋሚ እቃዎች እና የግንባታ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የሚያሟሉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. እቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን የንግድ ፍቃድ ያሳደሱ
  2. የ2019 ዓ.ም ግብር ያሳደሱ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ የተደራጁበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ እና በ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. Tin number ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. በገንዘብ ጽ/ቤት ለአቅራቢነት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ (በሲፒኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከገበያው ዋጋ በጣም ወርዶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
  9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሰነዱን በሐረማያ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን የጨረታውን ሰነድ በሚገባ በመሙላት አንድ ኦሪጅናልና 1 ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 6:30 ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ገፅ ሁሉ ላይ መፈረምና ማህተም ማሣረፍ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ

የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታውን ሰነድ ገዝቶ የሚሞላ የሚያቀርበው እቃ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥራቱ የተረጋገጠ መሆንአለበት፤

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0989794555 መጠየቅ ይችላል።

የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Haramaya Town Finance Office buys stationery, cleaning items, electronics, fixed items and construction materials by tender. Bidders need a renewed licence, 2019 tax payment, VAT, TIN and supplier registration with the finance office.
Save Tender