የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የመስተንግዶና HIV ሜኒስትሪሚንግ ግዥ በ7 ሎት በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ ሎት 2. የደንብ ልብስ ሎት 3. ህትመት ሎት 4. የፅዳት እቃ ሎት 5. ኤሌክትሮኒክስ ሎት 6.ቋሚ የቢሮ እቃ ሎት 7.መስተግዶ እና HIV ሜኒስትሬሚንግ ለ2019 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። በዚህም መሰረት:-
- ተጫራቾች ሕጋዊ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲን ነበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃ ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለባቸው።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚሞላው ዋጋ ከ500 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ኦሪጅናልና ኮፒዎችን በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ከ02/03/2019 ዓ.ም ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11/03/2019 ዓ.ም 11:30 ድረስ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የተዘጋጀውን የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱ መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 4 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 11/03/2019 ዓ/ም በማስገባት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ላይ ታሽጎ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰአት ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት የተቆረጠ ህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚያቀርቡ ከሆነ የቆይታ ጊዜው 60 ቀናና ከዚያ በላይ መሆን መቻል ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፤
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው ዕቃ ወይም ገንዘብ ላይ 30% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገ/ኢ/ት/ቢሮ ያወጣውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 44/2018 እና ተሻሽለው የወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ የመንግስትን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ካገኘው በተናጠልም የምናወዳድር መሆኑን መታወቅ አለበት።
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበው ዕቃ ጥራቱን የጠበቀ (ኦሪጅናል) ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለበት
- ለተጨማሪ መረጃ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት በስ/ቁ 033-551-29-61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kalu Woreda Court, Amhara, buys in seven lots by open tender: stationery, uniforms, printing, cleaning items, electronics, fixed office items, and hospitality and HIV mainstreaming items. Bidders need a renewed licence, TIN, paid tax and VAT for bids over 500,000.
