Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሞተር ሳይክል፣ ፈርኒቸርና ደንብ ልብስ በ5 ሎት በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች በሎት-01 የጽህፈት መሳሪያ በሎት-02 ኤሌክትሮኒክስ በሎት-03 ሞተር ሳይክል በሎት-04 ፈርኒቸር በሎት-05 ደንብ ልብስ- በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የስራ ፍቃድ፣
  2. የቫት/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. አግባብነት ያለውን የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ግዢ ክፍል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መወዳደር ይቻላል።
  5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ ስማቸውን፣ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት የሚችሉት በመ/ቤታችን በተዘጋጀው በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉንና ሁለት የኦርጅናሉ ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ CPO በኦርጅናል ቴክኒካል ፖስታ ውስጥ በማድረግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  9. ያስያዙት CPO ለወደቁት ሲመለስ ለአሸናፊዎች ግን ዕቃውን አቅርበው ሲጨርሱ ይመለሳል ።
  10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የዋጋ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  11. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የዕቃውን ናሙና አቅርቦ ተፈትሾና ተረጋግጦ በናሙናው መሰረት ዕቃው ኦርጅናል ብቻ ሲሆን ማቅረብ የሚችል ይሆናል።
  12. የጨረታ ስራን ሆን ብሎ ከጨረታ ማሸጊያ ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የጨረታ ስነ-ስርዓት ማወክና መረበሽ ከውድድር ውጪ ያደርጋል ፤በህግም ያስቀጣል።
  13. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ይከፈታል፤ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል።
  14. ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ዕቃውን ለማያቀርበው ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO አይመለስም።
  15. የዕቃው የመጨረሻ ርክክብ የሚፈጸመው ጨረታው በተካሄደበት በደቡብ/ም/ሲ/ህ/መንግስት በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል።
  16. የዕቃው ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ለሰበት።
  17. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ በሥ.ቁ 0473380451/59 መደወል ይችላሉ።
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ:- በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ስነ ሥርዓትን አያስተጓጉልም።

በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Wacha Town Finance Office, Kafa Zone, South West Ethiopia, buys for its sector offices in five lots by open tender: stationery, electronics, motorcycles, furniture and uniforms. Bidders need a renewed licence, VAT, TIN and supplier registration.
Save Tender