Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአይሲቲ፣ ኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ፣ የግንባታና የውሃ፣ የአውቶሞቲቭ፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ፣ የሆቴል ቱሪዝም እና የእንስሳት እርባታ የሥልጠና ዕቃዎችና ማሽነሪዎች በ6 ሎት በጨረታ ቁጥር ታፖቴኮ/04/2019 በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።

Tarcha polytechnic College (የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ/የጨረታ መለያ ቁጥር ታፖቴኮ/04/2019 ዓ.ም

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዘርፉ የተዘረዘሩትን የሥልጠና ዕቃዎችን በሃገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የአይሲቲ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና ማሽነሪዎች
  • ሎት 2. የግንባታ፣የውሃና ፈሳሽ መስመር፣ብረታ ብረትና ማሽነሪዎች
  • ሎት 3. የአውቶሞቲቭ ዕቃዎችና ማሽነሪዎች
  • ሎት 4 የጨርቃ ጨርቅ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና ማሽነሪዎች
  • ሎት 5. ሆቴል ቱሪዝም ዕቃዎች
  • ሎት 6. የእንስሳት እርባታ ዕቃዎች ማሽነሪዎች

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣

  1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለበት፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ አለበት፣
  3. የዘመኑ ግብር ስለመከፈሉ እና በጨረታ ይሳተፉ ደብዳቤን ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት፣
  4. የዕቃ ግዥ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ና በድረ-ገጽ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ አለበት፣
  5. የጨረታ ሰነድ ሦስት መቶ ብር ብቻ በኮሌጃችን የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000042580647 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው ከግ/ን/አስ/ዳ/ት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ላይ መግዛት ይችላሉ፣
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር ብቻ/ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ (CPO) በኮሌጃችን ስም በማዘጋጀት ከቴክኒካል መረጃ ፖስታ ጋር አንድ ላይ አሽጎ ማቅረብ አለበት፣
  7. ተጫራቾች የቴክኒካል መረጃ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ፣ የፋይናንሻል መረጃ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ሁሉንም መረጃ በአንድ እናት ፖስታ አሽጎ በግ/ን/አስ/ዳ/ት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው መክተት አለበት፣
  8. የጨረታ ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ከተቆጠረ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት ሥራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፣
  9. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተገባበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀን ነው።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዕቃ በገዙበት ሠነድ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር ግልጽ በሆነ በሚነበብ ጽሁፍ ሞልቶ ስምና ስልክ ቁጥራቸውን ጽፈው በድርጅታቸው ማህተምና በፊርማቸው ማረጋገጥ አለበት፣
  11. አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ ከኮሌጁ ጋር ውል መግባት ያለበት ሲሆን ዕቃውንም እስከ ኮሌጅ ግቢ ድረስ በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለበት። የጨረታ ማስታወቂያ የተጫራቾች መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፣
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Tarcha Polytechnic College, Dawro Zone, South West Ethiopia, buys training equipment in six lots: ICT and electrical, construction and plumbing, automotive, textile and leather, hotel and tourism, and livestock. Bidders need a renewed licence, VAT, TIN, tax clearance and supplier registration.
Save Tender