Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline19 Oct 2026, 4:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening dateጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Other Sales

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት እነ ሀብቴ ዓለሙ እና በፍርድ ባለእዳ እነ ምናሴ ዓለሙ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 278167 በ20/8/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በአዲስ አበባ በአራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 1039 የሆነውና በካርታ ቁጥር አ17/35/0800/02 በፍ/ባለእዳ አውራሽ አቶ ዘላለም መንግሥቱ ጓለ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ላይ እንደሰፈረው 692ካ.ሜ ይዞታው ከ4ኪሎ ሽሮሜዳ ጉለሌ እፅዋት ማእከል በተሠራው የኮሪዶር ልማት ፕላን ውስጥ ያለ አዋሳኞቹ በምስራቅ ቤተከህነት፣ በምዕራብ አቶ ታደሰ በደቡብ መንገድ በሰሜን ግርማ ወሰኔ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 29,696,566 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ አምስት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) ሆኖ የትራዛከሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከነ/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Auction sale by the Federal Courts Execution Office of a 692 sq.m property in Addis Ababa, Arada Sub-City, Woreda 09, House No. 1039. Bidders must submit a CPO for one-fourth of the starting estimate; the buyer pays transfer tax.
Save Tender