የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከቀን 07/01/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ለተሽከርካሪ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለመግዛት የሚያቀርበውን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በተለያዩ ባንኮች በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
- ተሽከርካሪውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
- ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸ ሊሰጣቸው ይችላል፤
- ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
- በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በቀን 11/01/2019 ከረፋዱ 3፡45 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።
- የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክመስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
NB:-
አሽናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ተሽከርካሪዎቹን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሆነ ኦክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ ሀላፊነቱን አይወስድም።
♦ የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Jigjiga Customs Office is selling various vehicles seized for contraband via open auction on the Auction Ethiopia platform. Any Ethiopian with a resident ID can participate by paying 100 birr for the bid document. Winners must pay immediately and collect within 5 days. VAT of 15% applies.
