ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ።
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር PPSVP-24EB/01/13/2019
የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ደምና ሕብር ህዋስ ባንክ አገልግሎት፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት፣ የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ የኢፌዴሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ የፌዴራል የሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፣ ኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የቤተ መንግስት አስተዳደር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ደን ልማት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።
- በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል።
- ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚገዙት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ነገርግን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር ያልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ነገር ግን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር ያልበለጠ/ ያላስያዘ እንዲሁም በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ ዕዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የጉምሩክ ቀረጥ ግብር እዳ፣ የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው የሚሸፈን ይሆናል።
- የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገባ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
- አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ፡- የተቋማችን ድረ-ገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ
የፌዴራል የመንግሥት ግዥ አገልግሎት
