Tender Detail

Tender Details


ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ.ማ መነሻ ግምታቸው ብር ከ12,000.00 የሆኑ የእርሻ መሳሪያዎች፣ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


እርሻ መሳሪያዎች ፣ኮንስትራክሽን መሻሪያዎች

 እና ተሽከርካሪዎች ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ኢማ መነሻ ግምታቸው ብር ከ12,000.00 የሆኑ የእርሻ መሳሪያዎች፣ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. የእርሻ መሳሪያዎች፣ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) ኩባንያው በሚገኝበት አዲስ አበባ ቦሌ ጄፓን ገነተ ልማት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 755 በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሚያወዳድሩበትን ዋጋ በመጥቀስና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ከሶስተኛው ቀን ጀምሮ ኩባንያው በሚገኝበት አዲስ አበባ ቦሌ ጄፓን ገነተ ልማት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 755 ሰዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  3. የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡05 ይከፈታል።
  4. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ በቅድሚያ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በገንዘብ ከፍያ ማዘዣ (ATA) ማስያዝ አለበት።
  5. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  6. የስም ዝውውር እና ሌሎች ተያያዥ በመንግስት የሚጠየቁ ወጪዎች ጨረታውን ባሸነፈው ተጫራች/በገዥው የሚሸፈኑ ናቸው።
  7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት የገዛበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
  8. ገዢው በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (አስራ አምስት በመቶ) መከፈል ይጠበቅበታል።
  9. ተጨማሪ መረጃ በ 0912 2370 9፣ 0915 66 66 66 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የእርሻ መሳሪያዎች፣ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ከፈለጉ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ይህ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን መመልከት ይችላሉ።
  11. ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

✨ messages.ai_summary
Ethio Sugar Manufacturing Industry invites bids for the sale of agricultural equipment, construction machinery, and vehicles. Bidders must submit a renewed residency ID with their offer and deposit 25% of the starting price via ATA payment order. The buyer covers name transfer and related government fees, plus 15% VAT.
Save Tender