የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ከፍያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት ኪራይ ለመከፈል ባለመቻሉ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በመጀመሪያ (1ኛ) ዙር በሐራጅ ደንበኛ ተመዝግበው ተከራይቶ የነበረውን ለመሸጥ
የመጀመሪያ (1ኛ) ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ከፍያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት ኪራይ ለመከፈል ባለመቻሉ በባንኩ ስም ተመዝግቦ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎች በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል ዕቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በመጀመሪያ (1ኛ) ዙር በሐራጅ ደንበኛ ተመዝግበው ተከራይቶ የነበረውን ለመሸጥ
| ተ.ቁ | የተከራዩ ስም | የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የሐራጁ መነሻ ዋጋ (በብር) | የንብረቱ ሁኔታ | ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት | የሐራጁ ደረጃ |
| 1 | ትዝታ፥ተሻለና ቤተሰቦቹ ዳቦና ኬክ አምራች ህብ/ሸር/ማህበር | 1. Rotary Over 16 Tray የዳቦ ማኮፈሻ አንድ(01) Set 2. Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ(01) set. 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4. Proofer For Rotary oven with Steam Generator (01) Set 5. Molding Machine Ar CX 70 (01) Set 6. Bread Slicer P (1) Set 7. French Bread Tray and Rottey for ATDF250 ሁለት(02) Set 8. Flat Tray with Trolley for ATDF 250 ሁለት(02) |
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሸገር ከተማ ገላን ከ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ | 9.373.294.86 | አዲስ | በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሸገር ከተማ ገላን ከ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ | ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 | 1ኛ |
የሐራጅ መመሪያ፡-
- የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲፒኦ በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይቻላል፡፡ በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በማቅረብ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ የሐራጅ ጨረታው ይካሄዳል፣
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግሥት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጅ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጅ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ በሐራጅ ጨረታ መሳተፍ ይችላል፡፡
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው
- በመንግሥት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል፡፡
- በሐራጅ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ተያያዥ የሆኑ ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው እጅ በእጅ በሚደረግ ሽያጭ/cash/ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሰራር በመከተል የሚደረግ ሽያጭ ይሆናል፡፡
- ንብረቱን በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል፡፡
- የካፒታል ዕቃ ካለበት መጋዘን ወደሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ የጉዞ ኢንሹራንስ፣ መትከያ፣ ሥራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ተከራይ ይሸፍናል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሐራጁን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከጨረታው ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ንብረቶቹን በሚገኙበት አድራሻ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-13659144 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Development Bank, Wolkite District, is auctioning repossessed leased capital goods (bakery machinery: rotary oven, dough divider, mixer, proofer, moulder, slicer, trays) as-is. Open to individuals, institutions, and SMEs with trade licence, TIN, and VAT registration.
