የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
– 6211 የደንብ ልብሶች 5,000.00
– 6212 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 15,000.00
– 6314 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 15,000.00
– 6218 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች 10,000.00
– 6215 አላቂ የትምህርት ዕቃና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች 15,000.00
– 6214 አላቂ የህክምና እቃዎች 4,000.00
– የደንብ ልብስ ስፊት 1,000.00
በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፤
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የከፋይነት ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል የምታቀርቡት ሰነድ ኮፒ ለእይታ የማያስቸግር ግልፅ መሆን ይኖርበታል፡፡
2. የንግድ ስራ ፈቃድ መስክ ጀርባ ይመልከቱ የሚለውን ኮፒ ጨምሮ ማቅረብ፤
3. ህጋዊ የካሽ ሬጂስተር ማሽን ደረሰኝ ወይም ህጋዊ በገቢዎች ፈቃድ የታተመ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ኪው አር ኮድ ያለው ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉት ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ባገኙበት መስክ ላይ ብቻ ይሆናል፣
5. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ክፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ከላይ በየሎቱ በተዘረዘረው መሰረት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ያሸነፋበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
8. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልፅ በመፃፍ እና ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በስራ ሰዓት በግዥ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
9. የዕቃውን ዋጋ ሲሞሉ ት/ቤቱ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት፤ ሰነዱ ላይ የስራ አስኪያጁ ፊርማ ማረፍ አለበት፣
10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና በንብረት ክፍል ማስገባት እና ተወዳድረው ባሸነፉበት እቃ ላይ ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው ማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን ቀይረው የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
11. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ አድራሻ የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታ ኮተቤ መሳለሚያ ዋርካ ት/ቤት አጠገብ ካራአሎ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0116-681280/0116-600470 ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ60 ቀናት ብቻ ነው፡፡
የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
