Tender Detail

Tender Details


በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በተፈቀደው መደበኛና ካፒታል በጀት በወረዳችን ውስጥ የሚገኙ በወረዳችን ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ ሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


2ተኛ ዙር ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/ቁ/07/2018

 

በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በተፈቀደው መደበኛና ካፒታል በጀት በወረዳችን ውስጥ የሚገኙ በወረዳችን ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ ሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ወረዳው የሚፈልጋቸው እቃዎች እንደሚከተለው በሎት ተከፋፍለው ቀርበዋል። ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት-2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-3 የደንብ ልብሶች፣ ሎት- 4 ሞተር ሳይክል ጎማና ከመነዳሪዎች፣ ሎት 5 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 6 ሞተር ሳይክል ጎማ፣ ሎት 7-የህንጻ መሳሪያዎች ሲሆኑ ይህ ጨረታ ግዥው ተግባራዊ የሚሆነው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ባወጣው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት ሆኖ የጨረታው ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን

1.     የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2.     ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የታደሰ የ2018 ንግድ ፈቃድ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ጋር አንድ የሆነ ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች በእቃ አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት በኦን ላየን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ / eGP /Electronic Government procurement ማቅረብ ይኖርባችኋል።

4.     የበጀት አመቱ ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ (የምስክር ወረቀት) ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2018 E.C))

5.     በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ መቅረብ አለባቸው።

6.     አሸናፊ ተጫራች ለግዥ ፈጻሚ የሚሰጠው ደረሰኝ የእጅ በዕጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከሆነ የንግድ ፈቃድ ባወጡበት ቦታ የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማህተም በጀርባው ሊኖረው ይገባል፣ አለበለዚያ የእጅ በዕጅ ሽያጭ ደረሰኝ ተቀባይነት የለውም።

7.     ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደ ሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል።

8.    ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ የዕቃ ብራንድ፤ የስሪት ዘመን፤ ሞዴል፤ የተመረተበት ሀገር እና ሌሎች ስለ ዕቃው መጠቀስ ያለበትን ነገር መግለፅ አለባቸው።

9.     እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የእቃዎቹ ዋጋ ሲሞላ ቫት ጨምሮ መሆን አለበት ካልጨመሩ እንደ ጨመሩ ታሳቢ ይደረጋል።

10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም።

11. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።

12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በመግቢያው ከተገለጹት ከሎት 1-5 በተዘረዘሩ የቋሚ እና አላቂ እቃዎች 7,000 /ሰባት ሺህ/ ብር፣ ሎት 6 እና 7 ብቻ 25,000 /ሃያ አምሰት ሺህ/ ብር፣ CPO ሲፒኦ (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ስም እውቅና ባለው ባንክ ህጋዊ ሲፒኦ ማሰራት አለባቸው።

13. የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት።

14. ተጫራቾች በአንድ እናት ፖስታ የእያንዳንዱ ሎት ሲፒኦ በማካተት በጥንቃቄ ታሸጎ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ (ቅጂ) ሰነድ በድርጅቱ ባለ ስልጣን የተፈረመበት እና በእያንዳንዱ ገጽ ማህተም የተደረገበት ሆኖ እስከ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ 06 በመምጣት ለፋይናንስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የሚመለከተው አካል በማሳወቅ በሳጥኑ መጨመር አለባቸው።

15. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የስራው ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ ከ11ኛ ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል።

16. የጨረታ ሳጥኑ ከ11ኛው / አስራ አንደኛ ቀን የህዝብ በዓል ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰአት በጨረታው ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8፡30 ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል።

17. መ/ቤታችን የሚፈልጋቸው ጥራታቸው የጠበቁ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዢ የምንፈጽምባቸው ወይም የምንረከበው በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ይሆናል።

18. አሸናፊ ከተለየ ውል ከተገባ በኋላ ግዢ የምንፈጽምባቸው እቃዎች መረከቢያ ጊዜ ግዢው ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ቀናት ውስጥ ይሆናል።

19. ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው ጥራታቸው የጠበቁ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል።

20. የቀረበው የመወዳደሪያ ሃሳብ (ዋጋ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ70 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ፤ መሆን አለበት።

21. በጨረታው ማስታወቂያና በጨረታ ሰነዱ መሃከል ልዩነት ከተፈጠረ የጨረታ ሰነዱ የበላይነት ይኖረዋል።

22. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመከፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት።

23. ተጫራቾች የጨረታው የመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ ቋንቋው በአማርኛ /በእንግሊዝኛ/ ነው።

 

ማሳሰቢያ ፡-

1.     ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታው በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

2.     አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ በ7ተኛው ቀን 10% ባሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት።

3.     የቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑንና

4.     የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 መሰረት ዊዝ ሆልድ 3% የምንቆርጥ መሆኑን አናሳስባለን።

5.     ከዚህ በፊት በአፈጻጸም ምክንያት በጽ/ቤታችን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እቃ ያላቀረቡ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር አይችሉም።

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0967441304/0921385494/0913205760

በአዲስ አበባ ሰነድ የሚሸጥበት ቀን ልክ ጨረታው ከታወጀበት ቀን አንስቶ 5 /አምስተኛው ቀን/ ድረስ መሆኑን

ስልክ ቁጥር፡- 0909067602/0973757244 ደውለው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

 

በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

Save Tender