የሲቪል ሰራተኛ አልባሳት፣ የቢሮ ፅህፈት እቃዎች፣ ጥራጥሬና የፋብሪካ ውጤቶች፣ የፅዳት እቃዎች እና የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ ግዥ (5 ሎት) - የ404ኛ ህዳሴ ኮር መምሪያ
የ404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ የ404ኛ ህዳሴ ኮር ግዥ ክፍል በ2019 በጀት አመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በሎት 1 የሲቪል ሰራተኛ አልባሳት፣ በሎት 2 የቢሮ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የትምህርትና ስልጠና መረጃ ዕቃዎች፣ የቅ/ፕሮፓጋንዳ እቃዎች፤ በሎት3 ጥራጥሬ እና የፋብሪካ ውጤቶች፤ በሎት 4 የፅዳት ዕቃዎች፤ በሎት 5 የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰርተፍኬት፣ ግብር ስለመከፈሉና ጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ ማስረጃ/በየወሩ ቫት ለመንግስት ገቢ ያደረገበት ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ 404ኛ ህዳሴ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ዴስክ ቢሮ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት ከጠቅላላ ዋጋ 2% በኋላ ላይ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በተገለፀው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ CPO በዕለቱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- ሎት 1 የሲቪል ሰራተኛ አልባሳት ብር--------8,000.00
- ሎት 2 የቢሮ የፅህፈት እቃዎች ብር--------65,427.36
- ሎት 3 ጥራጥሬ እና የፋብሪካ ውጤቶች-----100,324.24
- ሎት 4 የፅዳት ዕቃዎች ብር----------100,000.00
- ሎት 5 የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር ...... 30,000.00
ጨረታው ጥቅምት 18/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 03/2019 ዓ/ም በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በዚሁ ዕለት ህዳር 03/2019 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ህዳር 03/2019 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ዳቡስ ካምብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር / 0910212914 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አሶሳ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ የ404ኛ ህዳሴ ኮር መምሪያ
✨ messages.ai_summary
The Ministry of Defense's 404th Hidassie Corps seeks to procure, via open tender in five lots: civil servant clothing; office stationery, educational/training materials and propaganda items; cereals and factory products; cleaning supplies; and light vehicle spare parts. Bidders must hold a valid renewed business license, registration certificate, VAT certificate and proof of tax payments.
