በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
የሎት ቁጥር የሎት ዝርዝ የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር
ሎት 1 የደንብ ልብስ እና የፅዳት እቃዎች 6,000
ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የትምህርት እቃዎች 8,000
ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ እና ቋሚ እቃዎች 11,500
ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች እና ላብራቶሪ እቃዎች 3,450
ሎት 5 የግንባታ ዕቃዎች 4,000
ሁሉንም ሎቶች ለሚገዙ 32,950 (ሰላሳ ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ)
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶኮፒ ለየብቻው በማሸግ በየሎቱ የተዘጋጀውን የዋጋውን CPO በማካተት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአስረኛው (10ኛው) ቀን 11፡30 ሰአት ታሽጎ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ማቅረብ ለማይችሉት ቋሚ እቃ በፎቶ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116394253
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት
