በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 04 እውቀት ምንጭ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 7 በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-02/2018 ዓ.ም
በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 04 እውቀት ምንጭ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 7 በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 4 አላቂ የፅዳት እቃዎች
- ሎት 5 እላቂ የትምህርት መሳሪያዎች
- ሎት 6 የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 7 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 8 ህትመት ስራ
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች መሟላት ያለባችሁ ቅድመ ሁኔታዎች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከተደራጁበት ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ በመስሪያ ቤቱ ስም የተፃፈ ወቅታዊ የድጋፍ -ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
|
ሎት |
የእቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን |
|
1 |
የደንብ ልብስ |
5,000.00 |
|
2 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች |
5,000.00 |
|
3 |
ቋሚ እቃዎች |
5,000.00 |
|
4 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
3,000.00 |
|
5 |
አላቂ የትምህርት መሳሪያዎች |
5,000.00 |
|
6 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
3,000.00 |
|
7 |
ኤሌክትሮኒክስ ጥገና |
3,000.00 |
|
8 |
ህትመት ስራ |
3,000.00 |
- ለጨረታ ሰነድ ለሁሉም ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ እውቀት ምንጭ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት አሟልቶ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል ብሎ በመለየት በፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO) ውን እና ተያያዥ መረጃዎች ደግሞ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ ማስገባትና በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን በቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው በወጣበት 11ኛው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጠቅላላ ዋጋ 10 % እውቀት ምንጭ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ (CPO) ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይቻላል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በውሉ መሰረት በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል
ለተጨማሪ መረጃ
ስ.ቁጥር 0114162862/0114166823
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ መስመር ቡልጋሪያ ማዞሪያ ገባ ብሎ ኢንተርናሽናል ላብራቶሪ ክሊኒከ አጠገብ።
በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 04 እውቀት ምንጭ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
