በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ሎት-1 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 4 አነስተኛ ቋሚ እቃዎች፣ ሎት-5 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 6 ህትመቶች፣ ሎት-7 የስፖርት ደንብ ልብስ፣ ሎት-8 የስፖርት ቁሳቁስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ሎት-1 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 4 አነስተኛ ቋሚ እቃዎች፣ ሎት-5 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 6 ህትመቶች፣ ሎት-7 የስፖርት ደንብ ልብስ፣ ሎት-8 የስፖርት ቁሳቁስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው፣ የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ።
- ሎት 1 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት-3 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት-4 አነስተኛ ቋሚ እቃዎች፣ ሎት-5 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት-6 ህትመቶች፣ ሎት-7 የስፖርት ደንብ ልብስ፣ ሎት-8 የስፖርት ቁሳቁስ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በአካል (በወኪሎቻቸው) አማካኝነት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በመንግስት የሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ /ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመሂ፡ ያስያዙበትን ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራች ሙሉ ስም፣ ፊርማ፣ የድርጅቱን ማህተም፣ አድራሻ እና የግዥውን የእቃ አይነት/ሎት/ በመጥቀስ የጨረታ ማስከበሪያ የጽዳት እቃዎች 5000 ብር፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 3000 ብር፣ የፈርኒቸር እቃዎች 4,000 ብር፣ አነስተኛ ቋሚ እቃዎች 6000 ብር፣ የጽህፈት መሳሪያዎች 15000 ብር፣ ህትመቶች 3000 ብር፣ የስፖርት ደንብ ልብስ 1600 ብር እና የስፖርት ቁሳቁስ 7800 ብር በማስያዝ እና በጥንቃቄ በማሸግ በጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ከቀኑ 11፡30 /አስራ አንድ ሰዓት ተኩል/ ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን አስከ ጠዋቱ 3፡30 ማስገባት ትችላላችሁ። ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። (ተጫራቶች በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ባለመገኘታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም)።
- የጨረታ መክፈቻው በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን (ቅዳሜና እሑድ) ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ እና ለአገልግሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብርግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ቀንሶ ያስቀራል።
- ማንኛውም ኮፒ የሚደረጉ ማስረጃዎች በትከክል መነበብ እና መታየት አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውለታ በመፈጸም የግዥውን አቅርቦት ጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም ምንአልባት በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ሰረዝ አድርጎ ስለመሰረዙ ፊርማ ማስቀመጥ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሠረት በጥቅል /በሎት/ ነው። አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩት የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በተገለፀው ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔሲፊኬሽን መሰረት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መገለፅ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0946504962 በመደወል ማግኘት ይችላሉ። ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ.ሜ ርቀት በደሴ መስመር ላይ ነው።
በደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
