Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የደምብ ልብሶችን፣ ለጉዱሩ ፖሊ የቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የደምብ ልብሶችን፣ ለጉዱሩ ፖሊ የቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማሟሳት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

  1. በዚህ ስራ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት የተመዘገቡ መሆውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታውን ሰነድ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በጉዱሩ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር.4 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት መካከል በየቀኑ ከ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ማይከሮ ኢንተርፕራይዞች ይህን ማስከበሪያ፣ ዋጋ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ጉ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በመቅረብ ዋጋ ማቅረብያዎችን፡ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታው ሳጥን 15ኛው ስራ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉዱሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቁጥር 13 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታው ካሸነፉ በራሳቸው ወጪ እቃዉን በጉዱሩ ፐሊ የቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል ፡፡
  9. በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው የእቃው ብዛት (Quantity) 20% ለመቀነስም ሆነ ለመጨመር መስሪያ ቤቱ ሙሉ መብት አለው፡፡
  10. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር

0954558184, 0982246707, 0919496973

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉዱሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender