በአራዳ ክ/ከተማ የራስ እምሩ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የቢሮ ዕቃ፣ የጽዳት አላቂ ዕቃ፤ መድሀኒት የላብራቶሪ ግብዓት፣ ቋሚ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ ስፌት ህትመት፣ የተለያየ የሰርቪስ አገልግሎት ለማድረግ እና ከላይ የተዘረዘሩትን ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች መሸጥና ጥገናዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በአራዳ ክ/ከተማ ራስ እምሩ ጤና ጣቢያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/ቁ/01/2018
በአራዳ ክ/ከተማ የራስ እምሩ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የቢሮ ዕቃ፣ የጽዳት አላቂ ዕቃ፤ መድሀኒት የላብራቶሪ ግብዓት፣ ቋሚ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ ስፌት ህትመት፣ የተለያየ የሰርቪስ አገልግሎት ለማድረግ እና ከላይ የተዘረዘሩትን ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች መሸጥና ጥገናዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን 400.00 (አራት መቶ ብር) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ባሉት የስራ ቀናት በራስ እምሩ ጤና ጣቢያ ረዳት ፋይናንስ ክፍል 4ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
- በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው በስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በራስ እምሩ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 411 ባሉበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይንም ጨረታው ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል።
- ከገዙት ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒዮ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታውን ሲያስገቡ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝሩን እና ህጋዊ ማስረጃዎቹን የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ሲያስገቡ በታሸገ ፖስታ ውስጥ መሆን አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በተጫረቱበት ዕቃ ናሙና የማቅረብና ስፔሲፊኬሽን ለሚያስፈልገው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረቶች ወደ 4ተኛ ፎቅ ላይ ንብረት ክፍል ማስገባበት ግዴታ አለባቸው።
- የአገለገሉ ዕቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ባሉት የስራ ቀናት በራስ እምሩ ጤና ጣቢያ ረዳት ፋይናንስ ክፍል 4ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ጎጃም በረንዳ ዝቅ ብሎ በሲመንስ በኩል አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ በተለምዶ አባኮራን ሰፈር/ በግ ተራ
ለበለጠ መረጃ - ስልክ 01-11-26-67-12
በአራዳ ክ/ከተማ ራስ እምሩ ጤና ጣቢያ
