የመልሳ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት (በ2018 በጀት ዓመት ፍ/ቤቱ የሚጠቀመው አላቂ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ስቴሽነሪዎች እና የፅዳት ዕቃዎች ለፍ/ቤቱ የሚያገለግል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመልሳ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት (በ2018 በጀት ዓመት ፍ/ቤቱ የሚጠቀመው አላቂ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ስቴሽነሪዎች እና የፅዳት ዕቃዎች ለፍ/ቤቱ የሚያገለግል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ነጋዴዎች እና ባለሀብቶች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ስም አዘጋጅቶ ከማጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጥቃቅን እና አነስተኛ ማኅበራት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በመጥቀስ ካደራጃቸው መ/ቤት በቀጥታ ለመ/ቤታችን የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፣ የጥቃቅን እና አነስተኛ ማኅበራት ለጨረታ ማስከበሪያ ከቀበሌ የሚመጣ ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታ ለተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተሟላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡሉት ዋጋ ከትን 15 ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድርስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸፉትን ዕቃዎች ፍ/ቤቱ ካዘዘ በኋላ የታዘዘው ዕቃ አሸናፊው ለናሙና ለፍ/ቤቱ ማቅረብ የሚችል እና ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ ሲረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ከእሰቶካቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀኑ 8፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለፀው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ፍ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም ምርጫ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 251112601258
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
